Loading Events
ማስታወቂያ በምስረታ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት በዶሃ ከባለፈው ሀሙስ የካቲት 19 እስክ የካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም በነበሩት ሶስት ተከታታይ ቀናት በቀጣይ ዓመት ትምህርት የሚጀመርባቸውን የትምህርት ክፍሎች ብዛትና ደረጃዎችን በውል ለመለየት የተጀመረውን የተማሪዎች ቅድመ ምዝገባ አጠናክሮ መሄድ ይቻል ዘንድ የእድሳት ስራው በተጠናቀቀው የት/ቤቱ ህንጻ ቅጥር ጊቢ ውስጥ (Al Shahaniya) የወላጆች ጉብኝት እና የተማሪዎች ምዝገባ ማከናወኑ ይታወሳል በዚህ ዘመቻ የተገኙ ውጤቶችንና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ በየካቲት 23 ቀን 2012 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የትምህርት ቤቱ መስራች አብይ ኮሚቴ በዘመቻው በቀጣይ አመት ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችል በቂ የተማሪ ቁጥር መኖሩን ያረጋገጠ ሲሆን በጉብኝቱና ምዝገባው ላይ በንቃት ተሳትፎ ያደረጉ የተማሪ ወላጆችና ቤተሰቦች ምስጋናው አቅርቧል በትምህርት ቤቱ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልባቸው ክፍሎችና የትምህርት ደረጃዎች ላይ እና የወላጆች ሚናን አስመልክቶ ባስትላለፈው ውሳኔ
1. ለጊዜው ዝግጁ በሆኑት 3 የቅድመ መደበኛ ትምህርት መስጫ ክፍሎች /KG 1 + KG 2/ እንዲሁም አንደኛና ሁለተኛ ክፍል የተገኘውን ያህል ተማሪ በማስመዝገብ ትምህርት እንዲጀመር 2. በእስካሁኑ በላይ በተጠቀሱ የትምህርት ክፍሎችና ደረጃዎች ላይ ለመማር ምዝገባ ያላካሄዱ ተማሪዎች ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ቀን አንስቶ ባለው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የቅድመ ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ጥሪ እንዲተላለፍ 3. በትምህርት ቤቱ ላይ አይተኬ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የታመነባቸው ወላጆችና የወላጅ ቤተሰቦች ትምህርት ቤቱን በማስከፈት ሂደት ሚናቸውን በሚፈለገው ደረጃ መወጣት እንዲችሉ በአስር ቀናት ውስጥ ጊዜያዊ የወላጅ ኮሚቴ እንዲቋቋምና ከመስራች ኮሚቴው ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ ተወስኗል በመሆኑም በዶሃና አከባቢው ያላችሁና በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ ወላጆች በምዝገባው እንድትሳተፉ የቀረበውን የመጨረሻ እድል ከወዲሁ እንድትጠቀሙበት እንመክራለን ምዝገባውንም ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጠይቁን በመሙላት’ በስልክ ቁጥር +974-40207000/70190281 ዘወትር በስራ ሰዓት በመደወል አልያም በግንባር በሚሲዮኑና የኮሚኒቲ ጽ/ቤቱ የአገልግሎት መስጫ በመቅረብ ማከናወን የሚችሉ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን
This shortcode LP Profile only use on the page Profile
  • This event has passed.
  • Start Time
    12:00am
  • Finish Time
    11:59pm
  • Phone
    595-545-8575
  • Email
    info@yourmail.com
  • Organizer
    Barney Stinson

Registrations are closed for this event