

የፊታችን አርብ መጋቢት 04/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ልጆቻችሁን በኢትዮጵያ አለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት በዶሃ ለማስተማር ቅድመ ምዝገባ ላከናወናችሁ ወላጆች እንዲሁም ሌሎቻችሁ ለፊታችን ሃሙስ መጋቢት 03/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ለትምህርት ቤቱ ቁሳቁስ ማሟያ እንዲሆን በታሰበው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እንድትገኙ ጥሪ መተላለፉ ይታወሳል::
ይሁንና አሁን በቀጠር የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ከመቆጣጠር አንጻር እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ከመደገፍና የዜጎቻችንና የትምህርት ቤቱን ባለ ድርሻ አካላት ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር መሰል ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማራዘሙ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፕሮግራሞቹ ላልተወሰ ጊዜ መራዘማቸውን በአክብሮት እንገልጻለን::
ምንም እንኳን ለዚህ ሳምንት የተያዙት ፕሮግራሞች ላልተወሰ ጊዜ የተራዘሙ ቢሆንም ሌሎች ትምህርት ቤቱን በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ከKG እስከ 2ተኛ ክፍል ለማስጀመር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ግን ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማስታወቅ እንወዳለን::
በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት በዶሃ
መስራች ኮሚቴ
- This event has passed.
-
Start Time
8:00am -
Finish Time
5:00pm -
Website
View Organizer Website -
Phone
595-545-8575 -
Email
info@yourmail.com -
Organizer
Barney Stinson